+251 25 111 2233 info@diredawaedu.gov.et
Back to News
ዜና May 14, 2026 Dire Dawa Education Bureau

በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዎች ዝርዝር ተገለጸ

በድሬዳዋ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዎች ተገለጹ።

በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዎች ዝርዝር ተገለጸ

በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት «ተወዳዳሪ ትውልድ!» በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር በዛሬው ዕለት በምድብ 3 እና በምድብ 4 አሸናፊዎች መካከል በተደረገው የሁለተኛ ዙር ፍልሚያ በሁለቱም የትምህርት ዘርፎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ ተማሪዎች የገንዘብ ተሸላሚ የሆኑት ተማሪዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

📘 በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ (Social Science):-
🥇 1ኛ፡ እዮቤድ ሽመልስ (ከቤተ-ናታን ትምህርት ቤት)
🥈 2ኛ፡ ቦና ኢብራሂም (ከሳቢያን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
🥉 3ኛ፡ ኑራ አብዲ (ከድሬ ኤሊት ትምህርት ቤት)

🔬 በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ (Natural Science):-
🥇 1ኛ፡ ይዲዲያ እሸቱ (ከቅድስት ተሬዛ ትምህርት ቤት)
🥈 2ኛ፡ መንበረ አበበ (ከድሬዳዋ አጠቃላይ ትምህርት ቤት)
🥉 3ኛ፡ ማራናታ ማርቆስ (ከቅድስተ ማሪያም ካቴድራል ትምህርት ቤት)

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሸናፊ ተማሪዎችን "እንኳን ደስ አላችሁ! 👏" እያለ በቀጣይም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሰል አበረታች መድረኮችን ማዘጋጀቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ድሬዳዋ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

Share: